ማለዳ ማልደህ ስትነሳ እንዳዲስ ስጀምር ትናንትህን እረስተህ የዛሬህን ልትኖር ሆድህን ለመሙላት ለመጣር ለመልፋት ቀንህን ስጀምር ህይወትን ለመግፋት ትናንትህን እረስታህ ጨለማውን ክዳ ብቅ እንደምትለው የጠዋትህ ጀምበር እንደዛች ማለዳ ብቅ ብላ ብርሀን ፍካት ለጋሻችን ድቅድቅ ጨለማውን ገፋ ያሳየችን ተፈጥሮ አስተማሪ ተማሪ ጠፋ እንጂ አዋቂ ነኝ ባዩ ምሁሩ በዛ እንጂ ፎርሙላ ደርዳሪው ፊዚሻን ሞላ እንጂ ማች ጠፋና እንደኔ ተፈጥሮን ተረጂ አዎን ተረዳኃት የጀምበርን ሚስጥር የማለዳ ፍካት የማለዳ ፍካት የደማቀን ምስጢር አዎ እኔ እርሳ ነኝ የማለዳ ፍካት ትናንቴን ረግጩ በነገዬ ተስፋ የምኖር በትጋት መቀየር ቀላል ነው ስህተትን ረግጦ ያለፈውን ሸክም ማቃለል አራግፋ ወገኔ ተነስ በላ ተበረታ እንደ ማለደዋ ጨለማህን ግፈፋ ነገህን አበርታ!