كلمات Love
Hu Hu HAHAHA Ha Ha አትስሚው ኤቫና
ብቸኛ ነሽ አንቺ ማንም አይልሽ በርቺ ሁሌ ሚሉሽ ፍቺ
እመኚኝ ውድዬ በያ ተቀመጪ
አርፈሽ ሁሉን ትተሽ
ዝቅ ብለሽ አንሰሽ
ቆንጆ ነሽ ታምሪያለሽ የሚሉሽን ትተሽ
ውድዬ ታንሻለሽ ከሁሉም በታች ነሽ
ይሄን መራራ እውነት አምነሽ መቀበልሽ
ብቸኛው አማራጭሽ ከዚህ ውጪ የለሽ
አንቺ የበታች ነሽ በውነት የበታች ነሽ
ውድዬ እኔን ስሚኝ
በአትኩሮት አዳምጪኝ
ለሱ ጆሮ አትስጪው
ፊትም ጆሮም ንሺው
የበታች ለሚልሽ ተልቀሽ አሳፍሪው
በስኬት ድል ንሺው
ቆንጆ ነሽ አማላይ
በውበትም ገዳይ
እውቀትሽ የበዛ
ስላንቺ ሲወሳ
ሁሉም የሚመኝሽ
ለራሱ ለብቻው የግሉ ሊያደርግሽ
አዎ አንቺ የበላይ ነሽ እመኚኝ ኤቫና
የቁንጅና ፋና
የእውቀት ሁሉ ፋና
አንቺ ነሽ ኤቫና
እረረረረረ እኔን ስሚኝ
የእውነት ቃሌን ስሚኝ
በውሸት ሙገሳ
ሲያደርግሽ ፈዛዛ
ማየት አላስቻለኝ በውነት እኔን ስሚኝ
መልክሽን ተመልከች
መስታወት ፊት ቁመሽ
እውር የጋገረው ድፎ ዳቦ መስለሽ
እንዴት በዚ መልክሽ
ፍቅር ታስቢያለሽ
ሞኝ ነሽ ማመንሽ ያፈቅረኛል ብለሽ
ልጁ ነው የተመታ
እራሱን ያልቻለ
ፈዛዛ ደንጋዛ
ሚኒ ማኒሙ
አውቃለው ስለሱ ስላቺም በብዙ
ከቤት ተባሮ አይደል የተገኘው ካንቺ
ካንቺ ጋር ሲላላስ
ይሄን ጉድ ደብቀሽ
እውነታው እንዳይወጣ ላመታት ሸሽገሽ
እሁን ላይ Fame ስቶኝ እውቅናው ሲመጣ
Follower ሲንጋጋ በቲክቶክ ኢንስታ
ሁሉ የረሳው መስሎሽ cute couple ብለሽ
ትፖስቺ ጀመር ኖቪች በሚል ስምሽ
ayyy novichs በሚል ስምሽ!
ወጥ አትርገጥ ብሮ
ከመስመር አትውጣ በማይመለከትህ
የሰው ጎዳ አትግባ
እሱም ቢሆን እሳም ፍቅራቸው
የውነት ነው በእሳት ተፈትኖ ያለፈ ወርቅ ነው
አውጪው ከአንቺነትሽ አሉታዊ እሳቤን
አንቆ ያስቀረሽን መጥፋ ትንታኔ ን
ገመዱን በጥሽው ኃላ ሚያስቀርሽን
""ራስሽን ጥይው"" ደጋግሞ ሚልሽን
በአለማችን ያሉ ስኬት የጨበጡ
ጥቂት እድለኞች አለምን የገዙ
ሁሉም ሚስጥራቸው አንድ ነው ብቸኛ
ዕድል ወይ መተካት, ጥሮ ግሮ መስራት አይደለም ቁልፋቸው
""በራስ መተማመን"" ነው ayy ስኬት ያሳያቸው
ምክሮቼ ከገቡሽ ስሜትም ከሰጡሽ
በያ መልሺለት እወድሀለው ብለሽ
አፍቃሪን አትቅጪው በዝምታሽ ትተሽ
በያ መልሺለት ""እኔም"" ወድሀለው ብለሽ